የውሃ፡የውሃ ዲፕሎማሲና ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፎረም እየተካሄደ ነው

80

አርባምንጭ ሰኔ 02/2014 (ኢዜአ) ..... የውሃ፡የውሃ ዲፕሎማሲና ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፎረም በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው፡፡

ፎረሙ የተዘጋጀው አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ነው፡፡

በፕሮግራሙ የውሃ፡ የውሃ ዲፕሎማሲና ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፎረም የሚመሠረት ሲሆን የህዳሴ ግድብና የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ከዓለም አቀፍ እይታ አንጻር የመወያያ ጽሑፍ ቀርቦ እንደሚመከርበት ይጠበቃል፡፡

በፎሙ የውሃና ኢነርጂ ሚንስትር ዶክተር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ስለህዳሴ ግድብ እውነታ በስፋት እንዲያውቅ የሚገልፀውና የተወካዮች ምክር ቤት አባል መሓመድ አልአሩሲን ጨምሮ የተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ተወካዮች፡ ምሁራንና የሚዲያ አካላት  እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም