በአፍሪካ ቀንድ የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ በተሳካ ሁኔታ መቆጣጠር እንደተቻለ ተገለጸ

107

ግንቦት 29 ቀን 2014 (ኢዜአ)በአፍሪካ ቀንድ ባሉ ሀገራት የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ በተሳካ ሁኔታ መቆጣጠር እንደተቻለ ዩኒሴፍ አስታወቀ።

የዩኒሴፍ የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር ሞሀመድ ፋል በአፍሪካ ቀንድ የተከሰተው የበርሃ አንበጣ በተሳካ ሁኔታ መቆጣጠር ተችሏል ብለዋል።

ይህ ስኬት በቀጠናው የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም ትልቅ እርምጃ ነው ሲሉ የገለጹት ዳይሬክተሩ ባለድርሻ አካላት ወቅቱን በጠበቀ ሁኔታና ለአንድ አላማ ሲሰሩ ችግሮችን መሻገር እንደሚቻል አስገንዝበዋል።

ሌሎች ጉዳዮችንም በእንዲህ አይነት ርብርብ ማከናወን እንደሚገባ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም