የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የ2014 የስራ አፈጻጸም እየተገመገመ ነው

86

ግንቦት 29 ቀን 2014 (ኢዜአ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የ2014 አፈጻጸም በአዋሽ እየገመገመ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመሩት በዚህ መድረክ ላይ የእያንዳንዱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ያለፉት 10 ወራት አፈጻጸም ቀርቧል።

የአፈጻጸም ሪፖርቱን ያቀረቡት የፕላን እና ልማት ሚኒስትሯ ዶክተር ፍጹም አሰፋ፥ በዓመቱ ሀገሪቱ በውጫዊ እና ውስጣዊ ጫናዎች ውስጥ ብታልፍም ኢኮኖሚው እንቅስቃሴው ሳይስተጓጎል ማስቀጠል መቻሉን ተናግረዋል።

ለዚህም የበጋ ስንዴ፣ የሸቀጦች ወጪ ንግድ፣ ገቢ ምርትን በሀገር ውስጥ መተካት እንዲሁም የህዳሴ ግድብ ሀይል ማመንጨትን ጨምሮ በዓመቱ የተከናወኑ ስራዎች ትልቅ ፋይዳ ነበራቸው ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም