የታለመ የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ ተሸከርካሪዎች መለያ ስቲከር ይፋ ሆነ

157

ግንቦት 28 ቀን 2014 (ኢዜአ) የታለመ የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ የሚሆኑ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሸከርካሪዎች የታለመ የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ መሆናቸውን የሚገልፅ መለያ ይፋ ሆነ፡፡

የትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ሚኒስቴር እንደገለጸው፤ መለያው ሁለት አይነት ሲሆን ለመደበኛ ሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት ተሸከርካሪዎች እና በክልል ለሚገኙ ተሸከርካሪዎች የሚያገለግል ነው፡፡

መለያው ተሸከርካሪዎቹ የታለመ የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ መሆናቸውን ለነዳጅ ማደያዎችና  ለሚመለከታቸው ሌሎች አካላት መረጃ የሚሠጥ ነው፡፡

ሙሉ ሰማያዊ ቀለም ያለው መለያ ለሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት ተሸከርካሪዎች የሚያገለግል ሲሆን በነጭ መደብ የተዘጋጀው መለያ ደግሞ በክልል ለሚገኙ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎ ሰጪ ተሸከርካሪዎች የሚያገለግል ነው፡፡

በቅርቡ ተግባራዊ ለመሆን በዝግጅት ላይ የሚገኘው የታለመ የነዳጅ ድጎማ ስርዓት ተጠቃሚ የሚሆኑ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ተሸከርካሪዎችን የመለየትና መረጃ የማጥራት ስራ እየተከናወነበት እንደሚገኝ ይታወቃል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም