በአውሲ-ረሱ ዞን ኤሊደአር ከተማ ዛሬ ቀትር ላይ በተከሰተ የእሳት አደጋ የንብረት ጉዳት ደረሰ

273

ሰመራ፤ግንቦት 26/2014 (ኢዜአ)፡ በአፋር ክልል አውሲ-ረሱ ዞን ኤሊደአር ወረዳ ኤሊደአር ከተማ ዛሬ ቀትር ላይ በተከሰተ የእሳት አደጋ በንብረት ጉዳት መድረሱን የወረዳው ፓሊስ አስታወቀ።

የኤሊደአር ወረዳ ፓሊስ ወንጀል መከላከል ሃላፊ ዋናሳጂን አሊ ጋርዶ ለኢዜአ እንደገለጹት ዛሬ ከቀኑ 7 ሰዓት አካባቢ በወረዳው ኤሊደአር ከተማ ልዩ ስሙ ''ፈንቲ ማሃ ሰፈር'' በተባለ አካባቢ  ከንግድ ድርጅት የተነሳው ድንገተኛ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል።

የእሳት አደጋው በሰው ላይ ያደረሰ ጉዳት አለመኖሩንም ጠቁመው፤በአደጋ በአካባቢው በነበሩ መኖሪያ ቤቶችና የንግድ ድርጅቶች  ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።

የአደጋው መንስኤ ለግዜው አለመታወቁን ጠቁመው፤ የአደጋውን መንስኤና  በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት የማጣራ ስራ እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።

የእሳት አደጋውን የመከላከያ ሠራዊት አባላትና ህብረተሰብ ባደረጉት ርብርብ  የከፋ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር መዋል መቻሉን አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም