ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት የተለያዩ ሹመቶችን ሰጡ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት የተለያዩ ሹመቶችን ሰጡ

ግንቦት 26 ቀን 2014 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለከፍተኛ የመንግስት ሃላፊነት ቦታዎች ዛሬ የተለያዩ ሹመቶች ሰጥተዋል።
በዚህም መሰረት፤-
1. አምባሳደር ሬድዋ ሁሴን - የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር
2. አቶ ካሊድ አብዱራሀማን- በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የፕሮጄክቶች ክትትል
3. አቶ ወንድሙ ሴታ - የከተማና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ
4. አቶ ሄኖክ ወርቁ - የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬከተር
በተጨማሪም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤
የሚከተሉት ሹመቶች እንዲጸድቁ ጠይቀዋል፦
1. ወይዘሮ መሰረት ዳምጤ - የፌደራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ዋና ኦዲተር
2. አቶ አበራ ታደሰ - የፌደራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ምክትል ዋና ኦዲተር