የአውስትራሊያው ፍርተስኪ ፊዩቸር ኢንዱስትሪስ በኢትዮጵያ በዘርፉ ለመሠማራት የሚያስችለውን የኢንቨስትመንት ፈቃድ አገኘ

181

ግንቦት 25/2014( ኢዜአ)  የአውስትራሊያ የማዕድን ኩባንያ የሆነው ፍርተስኪ ፊዩቸር ኢንዱስትሪስ በኢትዮጵያ በዘርፉ ለመሠማራት የሚያስችለውን የኢንቨስትመንት ፈቃድ አገኘ።

በአረንጓዴ ኢንዱስትሪ ልማት ላይ የተሠማራው ይኸው ኩባንያ አረንጓዴ ሃይድሮጅንና አሞኒያ (ነዳጅ) የሚያመርት መሆኑ ተገልጿል፡፡

በኢትዮጵያም ያለውን ከፍተኛ የታዳሽ ኃይል ኃብት በመጠቀም የካርበን ልቀት የሌለው አረንጓዴ ሃይድሮጅንና አሞኒያ ልማት ላይ እንደሚሠማራም ተጠቅሷል።

ኩባንያው የሚያመርተው አረንጓዴ ሃይድሮጅንና አሞኒያ (ነዳጅ) ከፍተኛ ነዳጅ ኃይል ለሚጠቀሙ ኩባንያዎች፣ ተሽከርካሪዎች፣ ባቡሮችና ለአቬሽን ኢንዱስትሪ ግብዓትነት ይውላል ተብሏል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ፤ ኩባንያው በኢትዮጵያ ሥራ መጀመሩ አገሪቱ በታዳሽ ኃይል ላይ የተመሠረተ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት የምታደርገውን ጥረት ይደግፋል ብለዋል፡፡  

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም