የጤናው ዘርፍ የሰው ሀብት ፎረም በሐዋሳ እየተካሄደ ነው

103

ሐዋሳ፤ግንቦት 25/2014 (ኢዜአ)፡ ስምንተኛው ሀገር አቀፍ ዓመታዊ የጤናው ዘርፍ የሰው ሀብት ፎረም በሐዋሳ እየተካሄደ ነው።

የጤና ሚኒስቴር የጤና አገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመንና ለዘርፉ ጥያቄ ተገቢ ምላሽ ለመስጠት እንዲቻል እያካሄዳቸው ካሉ የሪፎርም ሥራዎች ውስጥ የሰው ሃይል አደረጃጀት መገንባት አንዱ መሆኑ ተመላክቷል።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው ፎረም የዘርፉን የሰው ኃይል በተሻለ መንገድ ለመገንባትና የላቀ ምላሽ ሰጪ የጤና ሥርዓት ለመዘርጋት በተዘጋጀው የሪፎርም ሰነድ ላይ ውይይት እንደሚደረግ ታውቋል።

በእስከ አሁኑ ሂደት የሰው ሃይል ልማት፣ የሰው ሀብት አስተዳደር፣ የጤና ባለሙያዎች ምዘና እና ፈቃድ አሰጣጥን የተመለከቱ ሰነዶች እየቀረቡ ነው።

በፎረሙ ላይ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አየለ ተሾመ፣ የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሰላማዊት መንገሻ እንዲሁም ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ የጤናው ዘርፍ አመራሮች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም