ኢትዮ ቴሌኮም 66 ትምህርት ቤቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የዲጂታል ትምህርት ማዕከል ፕሮጀክት አስጀመረ

473

ግንቦት 25 ቀን 2014 (ኢዜአ)ኢትዮ ቴሌኮም በአገር አቀፍ ደረጃ 66 ትምህርት ቤቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የዲጂታል ትምህርት ማዕከል ፕሮጀክት (Bridging divide digital center) አስጀመረ፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም በአዲስ አበባ ከፍተኛ 23 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዲጂታል ትምህርት ማዕከላት ኘሮጀክት አስጀምሯል፡፡

በዚሁ ወቅት የኢትዮ ቴሌኮም ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ተቋሙ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ተማሪዎች በትምህርት ቤቶች ቴክኖሎጂን በማወቅ ቢያድጉ የበለጠ ውጤታማ ይሆናሉ ብለዋል፡፡

May be an image of 1 person, sitting, standing and outdoors

ፕሮጀክቱ በአገር አቀፍ ደረጃ 66 ትምህርት ቤቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የዲጂታል ትምህርትን ነው ያስጀመረው፡፡

በዚህም 48 ትምህርት ቤቶች በክልሎች እና በአዲስ አበባ 18 መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዲጂታል ትምህርቱ 140 ሺህ 596 ተማሪዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ ብለዋል፡፡

ትምህርት ቤቶቹ ከዚህ በፊት የመሠረተ ልማት ችግር ያለባቸው ሲሆኑ በቀጣይ ከኢትዮ ቴሌኮም ስልጠና ይሰጣል ብለዋል፡፡

ለትምህርት ቤቶቹ የኮምፒውተርና የኢንተርኔት መሠረተ ልማቶች የተሟላላቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም