የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ በቶጎ ሎሜ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ቀጥታ በረራ እንደሚጀመር አስታወቀ

124

ግንቦት 24 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ በቶጎ ሎሜ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ከዛሬ ጀምሮ በሳምንት ሶስት ቀን ቀጥታ በረራ መጀመሩን አስታወቀ።

ከአዲስ አበባ ካይሮ በሳምንት አንድ ጊዜ የበረራ አገልግሎት በመስጠት ስራውን የጀመረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ወቅት 116 ዓለም ዓቀፍ መዳረሻዎች እንዲሁም 23 የአገር ውስጥ የበረራ መዳረሻዎች ያሉት ነው።

በቀውስ ጊዜ የራሱን ከፍታ አስጠብቆ መጓዝ የሚችል አየር መንገድ መሆኑን የኮረናቫይረስ ወረርሽኝ ዓለምን ባሰጋበት ወቅት በብቃት ያሳየው አየር መንገዱ ለሚሰጠው ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት በርካታ ዓለም ዓቀፍ ሽልማቶችን ያሸነፈ መሆኑ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም