የዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል የኩላሊት እጥበት ማዕከልን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ መረቁ

161

ግንቦት 22 ቀን 2014 (ኢዜአ)በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል የተገነባው የኩላሊት እጥበት ማዕከል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ተመረቀ።

አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ እየሰራ የሚገኝው የከተማ አስተዳደሩ ዘመናዊ ብቁ የጤና ተቋማት በመገንባት ተመጣጣኝና ፍትሀዊ የጤና አገልግሎትን ለመስጠት ትኩረት ሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።

ለኩላሊት ህመምተኞች እፎይታን ይሰጣል ተብሎ የሚጠበቀው በአሁን ሰአት ለምርቃት የበቃው በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ የተሰራው የኩላሊት እጥበት ማዕከል ቀድሞ በሁሉም የመንግስት ሆስፒታሎች ይሰጥ የነበረውን አገልግሎት በአምስት እጥፍ እንደሚያሳድገው ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም