የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም መሳካት ድጋፉን እንደሚያጠናክር ገለጸ

162

ግንቦት 20 ቀን 2014 (ኢዜአ) የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ስኬት የሚያደርግውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ።

ከዓለም ባንክ የተውጣጣ የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንፎርሜሽን ፕሮግራም ከሚተገብሩ መስሪያ ቤቶች ጋር በፕሮጀክቱ ትግበራ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

በቀጣይ የመሰረተ ልማት ግንባታ እና ተጨማሪ አዳዲስ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ማድረግ በሚቻልበት ዙሪያም መክረዋል።

የባንኩ የአይሲቲ ፖሊሲ መሪ እና የኢትዮጵያን የዲጂታል ፋውንዴሽን ፕሮጀክት የሚከታተሉት ቲም ኬሊ (ፒ ኤች ዲ) የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ስኬት የሚያደርግውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

የፕሮጀክቱ አፈፃፀም ላይ ማብራሪያ የሰጡት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ የዓለም ባንክ ፕሮግራሙ እንዲሳካ እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለኢዜአ በላከው መረጃ ገልጿል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም