የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከሐረሪ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ

172

ሐረር፣ ግንቦት 20 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከሐረሪ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ጋር በትብብር መስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ።

ስምምነቱን የተፈራረሙት የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጌትነት ታደሰና የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ሄኖክ ሙሉነህ ናቸው።

የሐረሪ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሄኖክ ሙሉነህ ስምምነቱ በአገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች በትብብር ለመስራት የሚያስችል ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጌትነት ታደሰ በስምምነቱ መሰረት ድርጅታቸው የክልሉን ገጽታ ሊገነቡ በሚችሉ ተግባራት እንዲሁም በክልሉ ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ስራዎችን ተደራሽ የማድረግ ስራ እንደሚያከናውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ያዘጋጀው የፎቶ ግራፍ አውደ-ርዕይ ዛሬ በሐረር ከተማ የተከፈተ ሲሆን ለአራት ተከታታይ ቀናት ይቆያል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም