በህልውና ዘመቻው ግዳጅ ላይ ቆይተው ለተመለሱ የደቡብ ልዩ ኃያል አባላት የእውቅናና የስትራቴጂክ አመራሮች ማዕረግ ማልበስ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በህልውና ዘመቻው ግዳጅ ላይ ቆይተው ለተመለሱ የደቡብ ልዩ ኃያል አባላት የእውቅናና የስትራቴጂክ አመራሮች ማዕረግ ማልበስ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው
ሀዋሳ፤ ግንቦት 20 ቀን 2014 (ኢዜአ) ኢትዮጵያን ለማዳን በተካሄደው የህልውና ዘመቻ ግዳጅ ላይ ቆይተው ለተመለሱ የደቡብ ክልል ልዩ ኃያል አባላት የእውቅናና የስትራቴጂክ አመራሮች የማዕረግ መልበስ ሥነ-ሥርዓት በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በዕውቅናና ማዕረግ ማልበስ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳውን ጨምሮ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስና የደቡብ ክልል ልዩ ኃይል ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የክልሉ፣ የዞንና ልዩ ወረዳ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
በመርሀ-ግብሩ የ1ኛ ፣ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃ የጀብድ ሜዳይ ተሸላሚዎች እውቅናና ሽልማት የሚሰጥ ሲሆን ጀብድ የፈፀሙ ልዩ ተሸላሚዎች ዕውቅና ይሰጣቸዋል ተብሏል።
በሀገራዊ ግዳጅ ወቅት የሕይወት መስዋዕትነት የከፈሉ የልዩ ኃይል አባላት ቤተሰቦችም ዕውቅናና ሽልማት የሚሰጣቸው እንደሆነ ተመላክቷል።