የመሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሌንሳ መኮንን በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ያፕራክ አልፕ ጋር ተወያዩ

310

ግንቦት 17 ቀን 2014 (ኢዜአ) የመሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሌንሳ መኮንን በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ያፕራክ አልፕ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም በዋናነት የቱርክ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ የሚሰማሩባቸውን የኢንቨስትመንት መስኮች መለየት ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡ 

ኮርፖሬሽኑ አሁን እየሠራቸው ስላሉ ተግባራት ለአምባሳደሯ ገለፃ መደረጉን የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር ሌንሳ መኮንን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

የቱርክ ባለሃብቶች ከኮርፖሬሽኑ ጋር በአጋርነት ሊሰማሩባቸው የሚችሉ የኢንቨስትመንት መስኮችን ለመለየት መግባባት ላይ መደረሱንም እንዲሁ፡፡

ኢትዮጵያና ቱርክ የኢንቨስትመንት ትስስራቸውን የሚጠናክሩበት ሁኔታዎችን ለመፍጠርና በቅርበት ለመስራት በውይይቱ ላይ ሀሳብ መለዋወጣቸውንም ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ የቱርክ ባለሃብቶች በአዳዲስ መስኮች እንዲሰማሩ ኮርፖሬሽኑ  ምቹ ምህዳር እንደሚፈጥርም ነው ዋና ዳይሬክተሯ ያረጋገጡት፡፡

በዚህም ሁለቱ አገራት በጋራ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ኮርፖሬሽኑ ከቱርክ ኤምባሲ ጋር ይሠራል ብለዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም