በሀረሪ ክልል ለከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ሲሰጥ የነበረው የመጀመሪያ ዙር የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ

159

ግንቦት 16 ቀን 2014 (ኢዜአ) በሀረሪ ክልል ለብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች "አዲስ ፖለቲካዊ እይታ - አዲስ አገራዊ እመርታ " በሚል መሪ ሀሳብ ሲሰጥ የነበረው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቋል።

በክልሉ በተካሄደው ስልጠና ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ እንደገለጹት ኢትዮጵያን ከፈተናዎቿ ሊያሻግር የሚችል ብቁ አመራር መፍጠር የብልጽግና ፓርቲ አንዱ አቅጣጫ መሆኑን ተናግረዋል።

አመራሩ አሁን እየገጠሙን ያሉ ተግዳሮቶችን በጽናት በመታገል ለሁለንተናዊ ብልጽግና መረጋገጥ በትጋት እንዲሰሩ አሳስበዋል።

በመጀመሪያ የፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ የተቀመጡ የሥራ አቅጣጫዎችን በዕቅድ በመያዝ ወደ ተግባር መገባቱን ገልጸዋል።

በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ከህብረተሰቡ ለሚነሱ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት በተጠናከረ መልኩ ሊሰሩ እንደሚገባ ገልጸዋል።

May be an image of 1 person and indoor

አመራሩ አቅሙን በማጎልበት ወቅቱን የሚመጥን አመራር መስጠት ይጠበቅበታል ብለዋል።

የክልሉን ህዝብ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በመልካም አስተዳደር ተጠቃሚ ለማድረግ የአመራሩ በቁርጠኝነት ሊሰራ እንደሚገባ አመላክተዋል።

አቶ አብዱጀባር አያይዘውም ተመሳሳይ የስልጠና መድረኮች እስከታችኛው የአመራር እርከን ተጠናከሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ለክልሉ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ያዘጋጀው ስልጠና ለአምስት ተከታታይ ቀናት ነው የተካሄደው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም