የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ለ220 ሴቶች ማዕድ አጋራ

126

ግንቦት 15 ቀን 2014 (ኢዜአ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ከአዲስ አበባ 11 ክፍለ ከተማዎች ለተውጣጡ 220 ሴቶች ማዕድ አጋርቷል።

በጽሕፈት ቤቱ ቅጥረ ግቢ የሚከናወነው የከተማ ግብርና የተጎበኘ ሲሆን፣ ፈጠራ በታከለበት መንገድ እንዴት መሠረታዊ አትክልቶችን ሁሉም በየቤቱ ለማምረት እንደሚቻል የሚያብራራ ማሳያ መሆኑም ተገልጿል።

በስነ ስርዓቱ ወቅት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ተፈሪ ፍቅሬ ቁሶችን መልሶ በጥቅም ላይ በማዋል የቦታ እጥረትን ቀርፎ የምንመገበውን ከደጃፋችን ማግኘትን ባህላችን ለማድረግ ያስፈልጋል በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።

የጓሮ ግብርናን በተመለከተ ሙያዊ እገዛ በክፍለ ከተማ፣ወረዳና ቀበሌ ደረጃ ለማግኘት እንደሚቻል አስታውቀዋል።

ሁሉም ሰው በተነሳሽነትና በኃላፊነት ምግቡን ከደጁ ለማግኘት እንዲሠራ ማበረታታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ

‼️

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ

‼️

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ

‼️

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

‼️
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም