የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ማኪ ሳል ወደ ዩክሬንና ሩስያያቀናሉ

ግንቦት 15 ቀን 2014 (ኢዜአ)የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበርና የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል በዩክሬንና ሩስያ መካከል የተፈጠረው ጦርነት በሰላማዊ መንገድ በሚፈታበት ሁኔታ ላይ ለመወያየት ወደ ሀገራቱ እንደሚያቀኑ አስታውቀዋል።

ማኪ ሳል በሩስያና በዩክሬን መካከል የተፈጠረው ውጥረት በውይይት እንዲፈታ የአፍሪካ ፍላጎት መሆኑን ገልጸዋል።

ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታትና ጦርነቱንም ለማስቆም የአፍሪካ ሕብረትን በመወከል ወደ ሩስያና ዩክሬን በቅርቡ እንደሚያቀኑ ማስታወቃቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል።

በዩክሬንና ሩስያ መካከል የሚካሄደውን ጦርነት በውይይትና በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶንዮ ጉተሬዝን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት መሪዎችና ባለስልጣናት ጉብኝትና ውይይት ማካሄዳቸው ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም