ለአብርሆት የመጽሐፍት ማሰባሰቢያ የሙዚቃና የኪነ ጥበብ ዝግጅት ሊካሄድ ነው

41

ግንቦት 13/2014 (ኢዜአ)  ለአብርሆት ቤተ መጽሃፍት፤ የመጽሐፍት ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር የሙዚቃና ኪነ ጥበብ ዝግጅት ሊካሄድ ነው።

የመግቢያ ዋጋው ለአንድ ሰው ሁለት መጽሐፍት መሆኑ ተገልጿል።

የአብሮሆት ቤተ መጽሐፍት ኃላፊ አቶ መስፍን ገዛኸኝ ለዚህ መርሃ ግብር ስኬትም የሙዚቃና የኪነ ጥበብ ዝግጅት ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

በግራዝማች ኢንተርቴይመንት አስተባባሪነት በሚካሄደው በዚህ መርሃ ግብር ለቤተ መጽሐፍቱ የሚያስፈልጉት 4 ሚሊዮን መጽሐፍት ለማግኘት ትልቅ እድል መሆኑን ተናግረዋል።

የሙዚቃና ኪነ-ጥበብ ዝግጅቱን ሰኔ 5 ቀን 2014 ዓ.ም ለማካሄድ መታሰቡን የግራዝማች ኢንተርቴይመንት ሥራ አስኪያጅ አቶ ብሩክ ግርማ ጠቁመዋል።

በዚህ የሙዚቃና ኪነ ጥበብ ዝግጅት 20 ሺህ መጽሐፍት ለማሰባሰብ መታቀዱን ገልጸዋል።

የመግቢያ ዋጋው ለአንድ ሰው ሁለት መጽሐፍት እንደሆነ ነው የተናገሩት።

በእለቱም ከመጽሐፍት ማሰባሰቡ ጎን ለጎን ለብሔራዊ ደም ባንክ አገልግሎት ከበጎ ፈቃደኞች ደም ለማሰባሰብ ታቅዷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም