10ኛው ሀገር አቀፍ የቱሪዝም ጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ በሠመራ ከተማ መካሄድ ጀመረ

65

ሰመራ፤ ግንቦት 13 ቀን 2014 (ኢዜአ) 10ኛው ሀገር አቀፍ የቱሪዝም ጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ "ቱሪዝም ለስራ-እድል ፈጠራ" በሚል መሪ ሀሳብ በሠመራ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

ኮንፈረንሱ በኢትዮጵያ ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዮት ከአፋር ባህልና ቱሪዝም ቢሮና ሠመራ ዩንቨርስቲ ጋር በመተባባር የተዘጋጀ ሲሆን አላማውም የክልሉን ዘርፈ-ብዙ የቱሪዝም ሃብት ማስተዋወቅና በጦርነትና ኮሮና ወረርሽኝ የተቀዛቀዘዉን የጎብኚዎችን ፍሰት ለማነቃቃት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በመድረኩም "ቱሪዝም በስራ እድል ፈጠራ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽና የአፋር ክልል ቱሪዝም ተጨባጭ ሁኔታ ፈተናዎችና መልካም አጋጣሚዎች" በሚል ጥናታዊ ጽሁፎች ለውይይት እንደሚቀርቡ ይጠበቃል።

በመድረኩ ላይ ቱሪዝም ሚኒስቴር፣የስራና ክሀሎት ሚኒስቴር አመራሮች የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዮት አመራሮች እንዲሁም የክልሉ ባህልና ቱሩዝም ሃላፊና የሰመራ ዩንቨርስቲ ፕሪዝዳንት ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም