የደቡብ ክልልን ከጎበኙ ቱሪስቶች 330 ሚሊየን ብር ገቢ ተገኘ

ሀዋሳ፤ ግንቦት 11/2014 (ኢዜአ) ባለፉት ዘጠኝ ወራት የደቡብ ክልልን ከጎበኙ ቱሪስቶች 330 ሚሊየን ብር ገቢ መገኘቱን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ፍሬህይወት ዱባለ ዛሬ ለኢዜአ እንዳስታወቁት ገቢው 

የተገኘው በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ የቱሪስት መስህቦችን ከጎበኙት መካከል   ከ27 ሺህ የሚበልጡት የውጭ ሀገር ጎብኝዎች መሆናቸውን ጠቁመው፤ ቀሪዎቹ የሀገር ውስጥ  ጎብኝዎች ናቸው ብለዋል።

በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ የቱሪስት መስህቦችን ለማስተዋወቅ በተካሄደው ጥረት የተገኘው 330 ሚሊየን ብር ከባለፉት ዓመታት ጋር ሲነጻጸር እድገት ማሳየቱን ተናግረዋል።

ቱሪዝምን ተከትሎ የሚመጡ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች ለማጠናከር ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በቱሪዝሙ ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ በዚህ ዓመት ብቻ ከ58 ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች 

ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል መፍጠር መቻሉን አስረድተዋል።

የአርባ ምንጭ አዞ እርባታ ማዕከል፣የኮንሶ መልከዓ ምድር፣የደቡብ ኦሞ የባህላዊ ክንዋኔ 

ስፍራዎች፣የማንጎ ብሄራዊ ፓርክን በክልሉ ከሚገኙ የቱሪስት መስህብ ስፍራዎች ግንባር ቀደም ተጠቃሾች መሆናቸው ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም