ባለፉት 10 ወራት ከ282 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

57

ግንቦት 11 ቀን 2014 (ኢዜአ) ባለፉት 10 ወራት 282 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።

የገቢዎች ሚኒስትር ላቀ አያሌው ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተቋሙን የስራ አፈጻጸም በሚመለከት ሪፖርት እያቀረቡ ይገኛሉ።

ሚኒስትሩ በሪፖርታቸው እንዳስታወቁት፤ ከአገር ውስጥ ገቢ እና ከወጪ ንግድ ቀረጥ በተሰበሰበ ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር 44 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ብልጫ አለው።

ከተሰበሰበው ገቢ ውስጥ 168 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብሩ ከአገር ውስጥ ገቢ ታክስ ሲሆን ቀሪው 113 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ደግሞ ከወጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ የተገኘ ገቢ መሆኑን አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም