ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ እና ለአቅም ደካማ ዜጎች የሚውል የቤት ግንባታ አስጀመሩ

136

ግንቦት 11 ቀን 2014 (ኢዜአ) ከንቲባ አዳነች አቤቤ የ40 ቤቶች ግንባታ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ዛሬ በሄንከን ኢትዮጵያ የገንዘብ ድጋፍ የሚገነባ የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ ፕሮጀክት አስጀምረዋል፡፡

ግንባታውም በ15 ሚሊዮን ብር የሚከናወን ሲሆን በ2 ወራት ውስጥ የሚጠናቀቅ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በዚሁ ወቅት ከንቲባ አዳነች እንዳሉት፤ ለከተማዋ ነዋሪዎች ምቹ የኑሮ ሁኔታ ለመፍጠር እየተሰራ ነው፡፡

May be an image of 4 people, people standing and outdoors

ለዚህም ከተማ አስተዳደሩ የአቅመ ደካሞች ቤት ዕድሳትን ጨምሮ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የከተማዋን ዕድገት ለማሳለጥ ከመንግሥት በተጨማሪ የህብረተሰቡ እንዲሁም የባለሃብቶች ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም