ቀጥታ፡

ወደ ፈረንሳይ በሕገ ወጥ መንገድ የገቡ የኢትዮጵያ ቅርሶች ወደ አገር ቤት ሊመለሱ ነው

ግንቦት 10 ቀን 2014 (ኢዜአ)ወደ ፈረንሳይ በሕገ ወጥ መንገድ የገቡ የኢትዮጵያ ቅርሶች ወደ አገር ቤት ሊመለሱ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በፓሪስ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የባህል ጉዳዮች የስራ ክፍልና ከፈረንሳይ ጉምሩክ ባለስልጣናት ጋር በጉዳዩ ላይ ፍሬያማ ውይይት ማድረጉን ገልጿል።

May be an image of 6 people, people standing and indoor

ባህላዊ እና ሐይማኖታዊ ቅርሶቹ እ.አ.አ መጋቢት 2019 በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ፈረንሳይ ሊገቡ ሲሉ በፓሪስ ራዮሲ አየር ማረፊያ የተያዙ መሆናቸው ተነግሯል።

በ15ኛው ክፍለ ዘመን የተሰራ መስቀል እንዲሁም በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ የተሰሩ የአንገት መደገፊዎች ከቅርሶቹ መሐል ይገኙበታል ተብሏል።

ወደ ሀገር ለመመለስም እ.አ.አ ሰኔ 2022መታቀዱንና የቅርሶቹ መመለስ ኢትዮጵያና ፈረንሳይ በባህል ዘርፍ ያላቸው የረጅም ጊዜ ጠንካራ ትብብር ማሳያ መሆኑን ሚኒስቴሩ አመልክቷል።

የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እ.አ.አ 2017 ቡርኪናፋሶን በጎበኙበት ወቅት በሕገ ወጥ መንገድ ወደ አገራቸው የገቡ የአፍሪካ ባህላዊ ቅርሶችን ለመመለስ ቃል መግባታቸው የሚታወስ ሲሆን፤የመንግስታቸው ዋንኛ የትኩረት አቅጣጫዎች አንዱ መሆኑን መናገራቸው የሚታወስ ነው።

“የአፍሪካ ቅርሶች በአውሮፓ የግል የስጦታ መሸጫ እቃዎችና ሙዚየሞች ሊቀመጡ አይገባም” ሲሉ በወቅቱ ገልጸው ነበር።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም