ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስና የገንዘብ ሚኒስቴር ኤፍኤስዲ አፍሪካ የኢትዮጵያ ሰነድ መዋዕለ ንዋዮች ገበያን ለማቋቋም የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

ግንቦት 10/2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ የሰነድ ሙዓለ ንዋዮች ገበያን ለማቋቋም የሚሰራ ፕሮጀክት በይፋ ስራ መጀመሩን የሚገልፅ ስምምነት በገንዘብ ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስና በኤፍ ኤስ ዲ አፍሪካ መካከል ተፈረመ።

የመግባቢያ ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ማሞ ምህረቱ እና የኤፍ ኤስ ዲ አፍሪካ ዋና ስራ አስፈጻሚ ማርክ ናየር ዛሬ በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል።

የሰነድ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ የግሉ ዘርፍና የመንግስት አጋርነትን በማጠናከር በባለሀብቶችና ቢዝነስን ለመገንባትና ለማስፋፋት ካፒታል በሚፈልጉ መካከል የፋይናንስ ልውውጥ ማዕከል እንደሚፈጥርም በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል።

በካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2013 ከተካተቱ ጉዳዮች መካከል በዛሬው ዕለት የሰነድ ሙዓለ ንዋዮች ገበያን ወይም (Ethiopian securities exchange) ለማቋቋም የሚሰራ ፕሮጀክት በይፋ ስራ መጀመሩን የሚገልፅ ስምምነት ነው ዛሬ የተፈረመው።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ በዚሁ ወቅት  እንዳሉት የኢትዮጵያ መንግስት በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርሙ ውስጥ የካፒታል ገበያን ለማስጀመር የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ነው።

በአዋጁ መሰረት ብሔራዊ ባንክ የካፒታል ገበያ ፕሮጀክት ትግበራ ቡድን አቋቁሞ የሰነድ ሙዓለ ንዋዮች ገበያን ለማቋቋም የሚያስችሉ ዝግጅቶችን ሲያደርግ መቆየቱን ጠቅሰዋል።

በካፒታል ገበያ አዋጁ መሰረት የሰነድ ሙዓለ ንዋዮች ገበያን (Ethiopian Securities Exchange) በመንግስትና በግሉ ዘርፍ የአክሲዮን ባለድርሻነት ለማቋቋም እየተሰራ ነው ብለዋል።

በመንግስት በኩል የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ገበያውን በዋና ባለድርሻነት ለማቋቋም ኃላፊነቱን የተረከበ ሲሆን በአክሲዮኑ የውጭ ባለሃብቶችም ባለድርሻ እንደሚሆኑ ነው የጠቆሙት።

በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው የሰነድ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ መቋቋም የግሉ ዘርፍና የመንግስት አጋርነትን በማጠናከር በተለይ ለፋይናንስ ዘርፉና በአጠቃላይ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ አዲስ ምዕራፍ እንደሚከፍት ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በሰነድ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ መቋቋም የግሉ ዘርፍና የመንግስት አጋርነትን በማጠናከር በተለይ ለፋይናንስ ዘርፉና በአጠቃላይ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ አዲስ ምዕራፍ እንደሚከፍት ጠቁመዋል።

ዋና ባለድርሻ መሆኑንም የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ማሞ ምህረቱ ተናገረዋል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የመንግስትን ስትራቴጂካዊ ግብ ለማሳካት ኢንቨስትመንት ማካሄድ፣ የመንግስት የልማት ተቋማትን እና ሀብትን ማስተዳደር፣ ወደ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት በሽርክና ለመሳብ ኃላፊነት  እንደተሰጠው ጠቅሰዋል።

ተቋሙ ዛሬ በተቋቋመው ፕሮጀክት እውን የሚሆነው ገበያ ዋና የሙዓለ ንዋይ ፈሰስ አድራጊ መሆኑንም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ስራ ፈጣሪዎች እና የቢዝነስ ሰዎች ስራቸውን ለማቀላጠፍ እንቅፋት ከሆኑባቸው ጉዳዮች ዋነኛው የፋይናንስ ብድር አቅርቦት ችግር መሆኑን ጠቅሰዋል።

ይህም ቢዝነሳቸውን እንዳያስፋፉና በቂ የስራ እድል እንዳይፈጥሩ አድርጓቸዋል ነው ያሉት።

ችግሩን ለመቅረፍና የረጅም ጊዜ የፋይናንስ አቅርቦት ለማመቻቸት የኢትዮጵያ የሰነድ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ መቋቋም የግሉ ዘርፍና የመንግስት አጋርነትን በማጠናከር በተለይ ለፋይናንስ ዘርፉና በአጠቃላይ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ አዲስ ምዕራፍ እንደሚከፍት ጠቁመዋል።

የገበያው መቋቋም በኢኮኖሚው ውስጥ ቁጠባንና ቢዝነስን የሚያበረታታ አሰራር እንዲኖር እንደሚያስችልም ተናግረዋል።

የብሔራዊ ባንክ ከፍተኛ የማክሮ ኢኮኖሚ አማካሪ አቶ መለሰ ምናለ እንደሚሉት፤ ባንኩ የባለሙያዎች ቡድን በማቋቋም የካፒታል ገበያን የሚቆጣጠር ባለስልጣንና የቁጥጥር ስርዓት ለማመቻቸት እየሰራ ነው።

ግብይትን የሚያሳልጡ ግለሰቦችና ተቋማት፣ አስማሚዎች፣ የኢንቨስትመንት ባንኮችና ሌሎችም አዲስ የሚቋቋመው ገበያ ተዋንያን እንደሚሆኑ ጠቅሰው፤ ለእነዚህ ባለድርሻዎች ፈቃድ የመስጠትና የቁጥጥር ስራን  ማን ይምራ የሚለው ማዕቀፍ እየተዘጋጀለት ነው ብለዋል።

ይህንን ወደ ስራ ለማስገባትም ቅድመ ዝግጅቶችን የሚሰራ ፕሮጀክት በዛሬው ዕለት መቋቋሙን አብራርተዋል።

ዛሬ በተፈረመው ስምምነት መሰረት ኤፍ ኤስ ዲ አፍሪካ (Financial Sector Deepening Africa) የሰነድ ሙዓለ ንዋዮች ገበያው መቋቋም የግሉ ዘርፍና የመንግስት አጋርነትን በማጠናከር በተለይ ለፋይናንስ ዘርፉና በአጠቃላይ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ አዲስ ምዕራፍ እንደሚከፍት ጠቁመዋል።

ምቹና ቀላል እንዲሆን የቴክኒክ ድጋፍ የሚደረግ መሆኑንም የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ ማርክ ናፒየር ተናግረዋል።

ገበያውን የማቋቋም ሂደቱ ተጠናቆ ስራ እስኪጀምር ድረስ ከመንግስት ጋር ተቀራርቦ መስራቱን ይቀጥላል ነው ያሉት።

የባለአክሲዮኖችን መብት መጠበቅን ማዕከል  ባደረገ መልኩ በሰነድ ሙዓለ ነዋዮች ገበያ ላይ ለመስራት በሚመዘገቡ አካላት ዘንድ መልካም የኩባንያ አስተዳደር ስርዓት እንዲኖር ለማድረግ ተገቢው ቁጥጥር እንደሚደረግም ተገልጿል።

የገበያው ምስረታ ሲጠናቀቅ በአፍሪካ 30ኛው የሰነድ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ይሆናል ተብሏል።

በገበያው ይፋዊ የሥራ መጀመሪያ ዝግጅት ላይ ባንኮችን የኢንሹራንስ ኩባንያዎችን ጨምሮ በትንሹ እስከ 50 ኩባንያዎች ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል።

የሰነድ ሙዓለ ንዋዮች ገበያው ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ለሆኑት አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የገቢ ማሰባሰቢያ መድረኮችን ለመፍጠር በሚያስችል መልኩ ተነድፏል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሀምሌ 16 ቀን 2013 ዓ.ም ባካሄደው ስብስባ የካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2013ን ማፅደቁ ይታወቃል።

አዋጁ ኢንቨስተሮችን ለመጠበቅና ገበያው ፍትሐዊ ተዓማኒና ቀልጣፋ እንዲሆን የሚያስችል የቁጥጥርና የበላይነት የመከታተያ የህግ ማዕቀፍ ለማዘጋጀት ያስችላል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም