በብልፅግና ፓርቲ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ቅርንጫፍ አመራሮች ስልጠና ተጀመረ

97

ግንቦት 10 ቀን 2014 (ኢዜአ)በብልፅግና ፓርቲ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ቅርንጫፍ አመራሮች ስልጠና ዛሬ ተጀምሯል።

የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ኢስሃቅ አብዱልቃድር እንዳሉት ስልጠናው ባለፉት ሁለት ዓመታት በጸጥታ ችግር ያጋጠሙ ፈተናዎችን በዘላቂነት መፍታት ላይ ያተኩራል።

የህብረተቡን ጥያቄ ለመመለስ በረጅም እና በአጭር ጊዜ እቅድ ሰነዶች ላይ ሰፊ ውይይት ይደረጋል ብለዋል።

የክልሉ የ10 ዓመት መሪ እቅድ ያለፉት ሁለት ዓመታት አፈፃፀም ዋነኛ ትኩረት እንደሆነ አስረድተዋል።

የስልጠናው ዋና ዓላማ በክልሉ መተከል እና ሌሎችም የተገኙ የሰላም ተስፋዎች በማስቀጠል እቅዱን በሚገባ ተግባራዊ ማድረግ እንደሆነ አስረድተዋል።

እንዲሁም ክልሉ ባለፉት ዓመታት ሲከተል የነበረው የኮሚዩኒኬሽን እና የሚዲያ አቅጣጫ እና የቀጣይ ትኩረቶችም ሌላው የስልጠናው ትኩረት መሆኑን አቶ ኢስሃቅ አስረድተዋል።

ከስልጠናው በተጨማሪ በተግባር የተከናወኑ የልማት ስራዎች የሚጎበኙ ሲሆን ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ተለይተው ተሞክሮ ይወሰድባቸዋል ብለዋል።

የፓርቲው አደረጃጀት እና ሌሌች ተያያዠ ጉዳዮችም ተካተዋል በስልጠናው።ስልጠናው የሚመራው በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጭምር እንደሆነ ሃላፊው አስታውቀዋል።

በክልሉ ስራ አመራር ማሰልጠኛ ተቋም በተጀመረው በዚሁ ስልጠና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ ከ200 የሚበልጡ እየተሳተፉ ነው።

ስልጠናው ለአምስት ተከታታይ ቀናት ይቆያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም