ሀገር አቀፍ የግጭት አዝማሚያዎችና መፍትሄዎች ላይ የሚመክር ጉባኤ በሚዛን አማን ተጀመረ

89

ግንቦት 10 ቀን 2014(ኢዜአ) በሀገሪቱ በተለያየ መልክ የሚከሰቱ የግጭት አዝማሚያዎችና ሊወሰዱ ስለሚገባቸው የመፍትሄ አቅጣጫዎች ላይ በተደረገው የዳሰሳ ጥናት ዙሪያ የሚመክር ጉባኤ በሚዛን አማን ከተማ ተጀመረ።

ጉባኤው የሰላም ሚኒስቴር ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።

በመድረኩም የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዷለምን ጨምሮ ሚኒስቴር ደኤታዎችን እንዲሁም ሌሎች የፌደራልና የሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የሰላም እና ፀጥታ ተቋማት ኃላፊዎችና የሚመለከታቸው አካላት በመሳተፍ ላይ ናቸው።

የሁለት ቀናት ቆይታ በሚኖረው በዚሁ መድረክ ሀገር አቀፍ የግጭት አዝማሚያና የመፍትሄ አቅጣጫ የሚጠቁም የዳሰሳ ጥናት ቀርቦ ምክክር የሚደረግበት እንደሆነም ታውቋል።

በመድረኩ የሚኒስቴሩ የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ላይ ውይይት ይደረጋል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም