የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ኡመር ሁሴን ከሌሎች የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በቃሉ ወረዳ በመስኖ እየለማ ያለ አትክልትና ፍራፍሬ ጎበኙ

ደሴ፣ ግንቦት 8/2014 (ኢዜአ) ግብርና ሚኒስትር አቶ ኡመር ሁሴን እና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ በመስኖ እየለማ ያለ አትክልትና ፍራፍሬ ጎበኙ ።

75 አርሶ አደሮች በ60 ሄክታር ማሳ ላይ በኩታ ገጠም እያለሙትን ያለው የአትክልትና ፍራፍሬ ማሳ ነው የጎበኙት።

የደቡብ ወሎ  ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ዓሊ ሰይድ እንደገለጹት በዞኑ በመስኖ እየለማ ካለው 23 ሺህ ሄክታር ውስጥ ከ5 ሺህ ሄክታር የሚበልጠው በአትክልትና ፍራፍሬ የለማ ነው።

አርሶ አደሮችን በኩታ ገጠም እንዲያለሙ በማድረግ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑንም  አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም