7ኛዉ ዙር የደቡብ ክልል የህብረት ስራ አውደ ርዕይ በሆሳዕና ከተማ ተከፈተ - ኢዜአ አማርኛ
7ኛዉ ዙር የደቡብ ክልል የህብረት ስራ አውደ ርዕይ በሆሳዕና ከተማ ተከፈተ
ሆሳዕና፣ ግንቦት 08 ቀን 2014 (ኢዜአ) 7ኛዉ ዙር የደቡብ ክልል አቀፍ የህብረት ስራ ኤግዚቢሽንና ባዛር (አውደ ርዕይ) "የህብረት ስራ ማህበራት ለተረጋጋ ገበያ" በሚል መሪ ቃል በሆሳዕና ተከፈተ።
መርሃ ግብሩ የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ አብዲ ሙመድን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ተከፍቷል።
የአውደ ርዕዩ አላማ በክልሉ የሚገኙ የህብረት ስራ ማህበራት የተለያዩ ግብርና ምርቶች በሆሳዕና ከተማ በማሰባሰብ ለአካባቢው ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብና ማስተዋወቅ መሆኑ ተገልጿል።
ምርቶችን በቀጥታ ለሸማች በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ገበያን ለማረጋጋትና የኑሮ ውድነትን ለማቃለል የሚደረገውን ጥረት መደገፍና ለማስፋት ተሞክሮዎች የሚወሰድበትም ነው ተብሏል።
ለሦስት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው በዚህ አውደ ርዕይ በህብረት ስራ ማህበራት ላይ በተገኙ ዉጤቶችና ተግዳሮቶች ላይ ምክክር ተደርጎ የመፍትሄ አቅጣጫ እንደሚቀመጥም ተመላክቷል።