ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሱፍሌት ማልት ኢትዮጵያ የተሰኘውን ብቅል አምራች ፋብሪካ መርቀው ከፈቱ

155

ግንቦት 5 ቀን 2014 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ60 ሚሊዮን ዩሮ የተገነባውን ሱፍሌት ማልት ኢትዮጵያ ብቅል አምራች ፋብሪካ መርቀው ከፈቱ።

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፓሬሽን ስር በሚተዳደረው በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የተገነባው ሱፍሌት ማልት ብቅል አምራች ፋብሪካ ነው የተመረቀው።

በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፓሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ ፤ የፋብሪካው አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።

በምረቃ ስነስርዓቱ ወቅት ፋብሪካው በአመት 60 ሺህ ቶን ብቅል የማምረት አቅም እንዳለው ተነግሯል።

ሱፍሌት ማልት ኢትዮጵያ የብቅል ፋብሪካ 10 ሔክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን በ 60 ሚሊዮን ዩሮ እንደተገነባ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን የተገኘው መረጃ ያሳያል።

ኢንቪቮ ግሩፕ በተባለ የፈረንሳይ ኩባንያ ስር የሚገኘው ሱፍሌት ማልት በ38 ሀገራት የተለያዩ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ፤ 90 የኢንዱስትሪ መንደሮች እና 13 ሺህ ሰራተኞች ያሉት ሲሆን በገነባቸው 28 የብቅል ማምረቻዎች በየአመቱ 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ቶን ብቅል ለአለም ገበያ እያቀረበ ይገኛል ተብሏል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ

‼️

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ

‼️

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ

‼️

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

‼️
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም