ቀጥታ፡

ኢዜአ “በሕልውናና በሕግ ማስከበር ዘመቻ” ላበረከተው አስተዋጽኦ በአማራ ክልል መንግስት የእውቅና ሽልማት ተሰጠው

ግንቦት 03 ቀን 2014 (ኢዜአ) የአማራ ክልል መንግስት የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) “በሕልውናና በሕግ ማስከበር ዘመቻ” ለነበረው አስተዋጽኦ የእውቅና ሽልማት አበረከተ።

ʺበሕግ ማስከበርና በሕልውና ዘመቻው የተከፈለ መስዋእትነት ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና አንድነት" በሚል መሪ ሃሳብ በዘመቻው አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት የእውቅና መስጠት ስነ ስርዓት በባህርዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) የተዘጋጀለትን የዋንጫ ሽልማት የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሰይፈ ደርቤ ከአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ተረክበዋል።

በእውቅና መርሃ ግብሩ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ዋልታ ሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ኮርፖሬት ሌሎች መገናኛ ብዙሃን የዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም