የአለም ጸረ ኤች አይ ቪ ኤይድስ ማስተባበርያ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ስለሚያደርግበት ሁኔታ ውይይት ተካሄደ - ኢዜአ አማርኛ
የአለም ጸረ ኤች አይ ቪ ኤይድስ ማስተባበርያ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ስለሚያደርግበት ሁኔታ ውይይት ተካሄደ
ግንቦት 03 ቀን 2014 (ኢዜአ) የአለም ጸረ-ኤች አይ ቪ ኤይድስ ማስተባበርያ በኢትዮጵያ ቤተ-ሙከራዎችን በማደራጀትና በሽታውን በመከላከል ረገድ ድጋፍ ስለሚያደርግበት ሁኔታ ውይይት ተካሂዷል።
የአለም ጽረ -ኤች አይ ቪ ኤይድስ ማስተባበሪያ የኢትዮጵያ ሃላፊ ዶክተር ካትሪን ጉድፍሬይ የተመራ ልዑክ በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ጉብኝት አካሂዷል።
በዚህ ወቅት የኢንስትቲዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው ቶሌራ ማስተባበርያው ለኢትዮጵያ ህብረተሰብ ኢኒስትቲዩት የቤተ-ሙከራ አቅርቦት ድጋፍ ስለሚያደርግበት ሁኔታ ምክክር አካሂደናል ብለዋል።
ማስተባበርያው ኬዝ ላይ የተመሰረተ የኤች አይቪ ኤድስ ክትትል ስራን ስለሚደግፍበት ሁኔታም መወያየታቸውን ገልጸው ልዑኩ ብሔራዊ የኤች አይ ቪ ቅንጣት ቤተ-ሙከራንና የተቋሙን የዘረመል ልዩ ልዩ ስራዎች ጎብኝቷል ነው ያሉት።