ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ ዓመታዊ መርሃ ግብር አስጀመሩ

179

ግንቦት 01 ቀን 2014 (ኢዜአ) ዛሬ ማለዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አዋሬ አካባቢ የሚኖሩ አቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ ዓመታዊ መርሃ ግብርን ማስጀመራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ገለጸ።

ጽህፈት ቤቱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ይፋ እንዳደረገው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ዓመታዊ እንቅስቃሴ ያስጀመሩት ከአራት ዓመታት በፊት የጠቅላይ ሚኒስትርነት ኃላፊነትን በተቀበሉበት የመጀመሪያ ዓመት ነው።

የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ ዓመታዊ መርሃ ግብር አላማ የአረጋውያን፣ የአቅመ ደካሞች፣ የአካል ጉዳተኞች እና በኢኮኖሚ የተቸገሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን መኖሪያ ቤት ማደስ እንደሆነ ገልጿል።

መርሃ ግብሩ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ፣ በየዓመቱ ክረምት ከመግባቱ በፊት የቤት እድሳት መርሃ ግብር ሲከናወን መቆየቱን አመልክቷል።

በዚህ አመት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ 'የመደመር መንገድ' ከተሰኘው መጽሃፋቸው ሽያጭ በተገኘ ገንዘብ በአዋሬ አካባቢ ተለይተው ለታወቁ 23 ግለሰቦች የመኖሪያ ቤት ግንባታ የሚደረግበትን ሂደት ዛሬ አስጀምረዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም