ቀጥታ፡

የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከነገ ጀምሮ ስብሰባ ያካሄዳል

አዲስ አበባ ጳጉሜ 2/2010 የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከነገ ጳጉሜ 03 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰበሰብ የኢሕአዴግ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት የሕዝብና ውጭ ግንኙነት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ሳዳት ነሻ አስታውቀዋል። ስራ አሰፈፃሚ ኮሚቴው ከሁለት ሳምንት በፊት አካሂዶት በነበረው መደበኛ ስብሰባ ወቅት ከተወያየባቸው አጀንዳዎች በተጨማሪ መታየት ሲኖርባቸው በጊዜ እጥረት ምክንያት ባልተዳሰሱ ድርጅታዊና ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ እንደሚመክር ይጠበቃል። በተጨማሪም በ11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ ላይ በሚቀርበው የድርጅቱ ሪፖርት ላይ የሚወያይ ሲሆን አጠቃላይ የጉባኤ ዝግጅቱ ያለበትን ሁኔታ በመገምገም የቀሪ ስራዎች አፈፃፀም አቅጣጫን ያስቀምጣል። ኮሚቴው በቅርቡ ባደረገው ስብሰባ እየተወሰዱ ያሉ አገራዊ የለውጥ እርምጃዎችን እንዴት አጥናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት ተወያይቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን ማሳለፉ ይታወሳል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም