የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት 20 ሚኒስትሮች ያካተተውን አዲሱን ካቢኔያቸውን ይፋ አደረጉ

93
ጳጉሜ 2/2010 ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ በፈረንጆቹ ሃምሌ 30 የተካሄደውን ምርጫ ማሸነፋቸውን ተከትሎ 20 ሚኒስትሮችን ሹመዋል። ከዚህ ቀደም የነበሩትን 33 የካቢኔ አባላት ቁጥርም ወደ 33 ዝቅ ያደረጉ ሲሆን ስምንት አዳዲስ ሚኒስትሮችም ወደ ስልጣን መጥተዋል ነው የተባለው። የቀድሞው የአፍሪካ ልማት ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት ምቱሊ ንኩቢ የፋይናንስ ሚኒስትር ሆነዋል። የቀድሞ የውሃ ዋና ዓለም አቀፍ ሻምፒዮን ኪርስቲ ኮቬንትሪ ደግሞ የስፖርትና ኪነጥበባት ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል። ፕሬዚዳንት ምናንጋግዋ የዛኑ ፒ ኤፍ ፓርቲ ሊቀመንበር ኦፓህ ሙቺንጉሪን የመከላከያ ሚኒስትር አድርገዋል። ሲቡሲሶ ሞዮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔሬንስ ሺሪ የግብርና ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል። ሆኖም በአዲሱ ካቢኔ ውስጥም ነባር ባለስልጣናት ስለሚበዙ ለውጥ የለም የሚል ትችት እየተሰነዘረ ነው። ሌሎች ደግሞ ፕሬዚዳንት ምናንጋግዋ የነባሩን ስርዓት ሚዛናዊ በሆነ መንገድ እየለወጡት ነው የሚል አስተያየት ሰንዝረዋል። ምንጭ፦ቢቢሲ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም