የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤትና የመሰናዶ ትምህርት መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ

232
አዲስአበባ ጳግሜ 2/2010 የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትና ወደ መሰናዶ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ። የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርዓያ ግብረእግዚብሄር በሰጡት መግለጫ፤ የ2010 ዓ.ም የ10ኛ ከፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች ውጤት ከዛሬ ምሽት 12 ሰዓት ጀምሮ ይለቀቃል። 7ሺህ201 ተማሪዎች አራት ነጥብ አምጥተዋል። ዋና ዳይሬክተሩ በመግለጫው ላይ ይፋ እንዳደረጉት ወደ 11ኛ ክፍል ማለፊያ የመቁረጫ ነጥብም ይፋ አድርገዋል። በዚህም ትምህርታቸውን በመደበኛና በማታ ለተከታተሉ ተፈታኞች ለወንዶች 2 ነጥብ 71፣ ለሴቶች 2 ነጥብ 57 ሲሆን ለግል ተፈታኞች ለወንድ 3 ነጥብ 43፣ ለሴት 3 ነጥብ 14 መሆኑን ተናግረዋል' ለአርብቶ አደርና ታዳጊ ክልሎች ተፈታኞች ደግሞ ለወንዶች 2 ነጥብ 43 ለሴቶች 2 ነጥብ 29 ሲሆን ለአይነ ስውራንና መስማት ለተሳናቸው ተፈታኞች ለወንድ 2 ነጥብ 14፣ ለሴት 2 ነጥብ መሆኑን ይፋ አድርገዋል። በ2010 የትምህርት ዘመን የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከወሰዱ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ተማሪዎች መካከል 636 ሺህ 106 በላይ ተማሪዎች ከ2 ነጥብ በላይ አምጥተዋል። በመቁረጫ ነጥቡ መሰረትም 350 ሺህ ተማሪዎች ወደ መሰናዶ ትምህርት እንደሚቀላቀሉ ታውቋል። ተፈታኞቹ ውጤታቸውንም ከዛሬ ጳጉሜ 2 ቀን 2010 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በመልዕክት 8181-Rtn- የፈተና መለያ ቁጥር ወይም በኤጀንሲው ድረ ገጽ www.neaea.gov.et መመልከት እንደሚችሉ አስታውቋል።                
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም