ቀጥታ፡

አምባሳደር ታዬ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር ውጤታማ ውይይት አደረጉ

ሚያዝያ 26 ቀን 2014 (ኢዜአ) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሀና ሰርዋ ቴቴ ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ገለጹ፡፡

አምባሳደር ታዬ በውይይቱ ወቅት በቀጣናው ወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች፤በኢትዮጵያ የሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽ እንዲሆን በተወሰደው የተኩስ ማቆም ውሳኔ እና ወቅታዊ ሁኔታዎች ፤በቀጣናው ባሉ ድንበር ዘለል የፀጥታ ፈተናዎች እና መሰል ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም