ከነገ ጀምሮ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የጸጥታ ተቋማት እና ልማት ፕሮጄክቶችን ይጎበኛሉ - ኢዜአ አማርኛ
ከነገ ጀምሮ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የጸጥታ ተቋማት እና ልማት ፕሮጄክቶችን ይጎበኛሉ
ሚያዚያ 24 ቀን 2014 (ኢዜአ) ከነገ ጀምሮ እስከ ሳምንቱ መጨረሻ ቀን ድረስ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የጸጥታ ተቋማት እና ልማት ፕሮጄክቶችን ይጎበኛሉ።
ከዚህ ቀደም በሚያዚያ ወር መጀመሪያ ላይ የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች እና የመከላከያ ጀነራሎች የጸጥታ ተቋማት እና ልማት ፕሮጄክቶችን መጎብኘታቸው ይታወሳል።
በጉብኝታቸውም የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ መረጃ መረብ አገልግሎት (ኢንሳ) እንዲሁም የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትን መጎብኘታቸው ይታወሳል።