ቀጥታ፡

ሰላም፣ መተሳሰብና መከባበር መገለጫችን ሊሆን ይገባል --ኡስታዝ አቡበከር አህመድ

ሚያዚያ 24/ 2014 (ኢዜአ) ሰላም፣ መተሳሰብና መከባበር እንደቀድሞው ሁሉ ዛሬም መገለጫችን ሊሆን ይገባል ሲሉ የእስልምና ሃይማኖት መምህር የሆኑት ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ተናገሩ፡፡

በመሆኑም ክፋትን በክፋት፣ ጥፋትን በጥፋት እንድንመለስ የታዘዝን ህዝቦች አይደለንም ሲሉም ነው የተናገሩት፡፡

ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ይህን ያሉት በታላቁ የኢድ ሰላት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ነው።

በመልዕክታቸውም እስልምና መሰረቱ ሰላም መሆኑን ጠቅሰው፤ ከዚህ አኳያ ሰላም፣ መተሳሰብና መከባበር እንደቀድሞው ሁሉ ዛሬም መገለጫችን ሊሆን ይገባል ነው ያሉት፡፡

ህዝበ ሙስሊሙ የሚታወቀው በፍትህ፣ እኩልነት እና ለሌሎች ተስፍ በመሆን ነው ብለዋል።

ሰሞኑን በተለያዩ በተፈጠረው እኩይ ድርጊት አዝነናል፣ መንግስት አጥፊዎችን በአስቸኳይ ለህግ ሊያቀርብ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ህዝበ ሙስሊሙም በእስልምና አስተምህሮ መሰረት ለሰላም መትጋት እንዳለበትም ጥሪ አቅርበዋል።

ሰላም ተግባራችን መገለጫችን ሊሆን ይገባል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም