ጥፋትን በጥፋት ነውርን በነውር አናክመውም – ኡስታዝ አቡበከር - ኢዜአ አማርኛ
ጥፋትን በጥፋት ነውርን በነውር አናክመውም – ኡስታዝ አቡበከር
ሚያዚያ 21 ቀን 2014 (ኢዜአ) ሰሞኑን መሆን የማይገባቸው ነገሮች ሆነዋል፤ ይሁንና ጥፋትን በጥፋት ነውርን በነውር አናክመውም ሲሉ ኡዝታዝ አቡበከር አህመድ ተናገሩ።
ኡዝታዝ አቡበከር አህመድ ይህን ያሉት በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው ታላቁ የኢፍጣር መርሃ ግብር ላይ ነው።
በወቅቱ እንዳሉትም በህዝብ ላይ ነውረኛ ተግባር የሚፈጽሙ አካላት ተገቢው ህጋዊ ቅጣት ይገባቸዋል።
ጥያቄያችንን በሰላማዊ መንገድ በማቅረብ ችግሮች እንዲፈቱ ጥረት ማድረግ አለብን ሲሉም አስገንዝበዋል።
እስልምና በሚያዘው መሠረትም ነገሮችን ማስኬድ እንደሚገባም አስረድተዋል።