ጉባዔው የኦሮሞን ህዝብ ጥያቄ ፍላጎትና ጥቅምን መሰረት ያደረገ ነው- ወይዘሮ አዳነች አቤቤ

82
ጳጉሜ 2/2010 9ኛው የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ጉባዔ የኦሮሞን ህዝብ  ጥያቄ፤ ፍላጎትና ጥቅም መሰረት ያደረገ ነው ስሉ  የኦህዴድ ማእከላዊ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ አስታወቁ፡፡ የድርጅቱ ማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ መጠናቀቅን አስመልክቶ  የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ በሰጡት መግለጫ፥ 9ኛው የኦህዴድ ድርጅታዊ ጉባዔ ከመስከረም 8 እስከ 10  ቀን 2011 ዓ.ም እንደሚካሄድ ተወስኗል፡፡ ጉባኤው የኦሮሞ ህዝብ ትግል ወሳኝ ምእራፍ ላይ በደረሰበት ወቅት የሚካሄድ በመሆኑ ታሪካዊ ያደርገዋል በማለት ተናግረዋል። ኦህዴድ የኦሮሞን ህዝብ ትግል በመምራት ለድል ያበቃ ድርጅት መሆን ገልጸው  የተመዘገበውን ለውጥ ሳይሸራረፍ በማስቀጠል የበለጠ  ድል ለማስመዝገብ ድርጅታቸው ከፍተኛ ብቃትና ዝግጅት ላይ እንደምገኝም ወ/ሮ አዳነች  ተናግረዋል፡፡ የተገኘውን ለውጥ በብቃት ለመምራትም በኦህዴድ 9ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ ላይ የሚሳተፉ አባላት ያላቸው እውቀት፣ ብቃት እና ተቆርቋሪነት ላይ ተመስርቶ በትኩረት ሊመረጡ እንደሚገባ ማእከላዊ ኮሚቴው አቅጣጫ ማስቀመጡን  ኃላፊዋ አስገንዝበዋል፡፡ ማእከላዊ ኮሚቴው በስብሰባው ማጠቃለያ ላይም የድርጅቱ የትግል ደረጃ፣ የኦሮሞን ባህል እና ወግ መሰረት በማድረግ የኦህዴድን ስያሜ፣ ሎጎ፣ መዝሙር እንዲሁም የመተዳደሪያ ደንብን ለመለወጥ በቀረበው ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ ላይ በመወያየት በድርጅታዊ ጉባዔው ለውሳኔ እንዲቀርብ አቅጣጫ ማስቀመጡንም  ተናግረዋል። ምንጭ፡- ኦ ቢ ኤን          
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም