ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከደቡብ አፍሪካ አቻው ጋር የፊታችን እሁድ ጨዋታውን ያደርጋል

ሚያዚያ 21/2014/ኢዜአ/ በህንድ ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ውድድር የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ሶስተኛ ዙር የመልስ ጨዋታውን ከነገ በስቲያ በአበበ በቂላ ስታዲየም ያደርጋል።

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሜዳው ውጭ ደቡብ አፍሪካን 3 ለ 0 አሽንፎ መመለሱ ይታወቃል።

ብሔራዊ ቡድኑ የፊታችን እሁድ ደግሞ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የመልስ ጨዋታቸውን ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ያደርጋሉ።

በአሰልጣኝ አንዳልካቸው ጫካ የሚመሩት የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በሜዳቸው በሰፊ የጎል ልዩነት በደርሶ መልስ ድምር ውጤት የሚያሸንፍ ከሆነ ለመጨረሻው የአራተኛ ዙር የማጣሪያ ጨዋታ የሚያልፍ ይሆኖል።

በአራተኛ ዙር የሚያገኘውን ቡድን ደግሞ በደርሶ መልስ ድምር ውጤት ማሸነፍ ከቻሉ የዓለም ዋንጫውን ትኬት የሚቆርጡ ይሆናል።

በ2022 ዓ.ም በህንድ ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ሶስተኛ ዙር ጨዋታ በአፍሪካ 12 ሀገራት እየተፎካከሩ ሲሆን በደርሶ መልስ አሸናፊ የሆኑ ስድስት ሀገራት ወደ አራተኛ ዙር የሚያልፉ ይሆናል።

በአራተኛ ዙር ጨዋታ አሸናፊ የሆኑ ሶስት የአፍሪካ ሀገራት በዓለም ዋንጫው የሚካፈሉ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም