በሆርቲካልቸር ዘርፍ ከ200ሺህ በላይ የሥራ እድሎች ተፈጥረዋል - ኢዜአ አማርኛ
በሆርቲካልቸር ዘርፍ ከ200ሺህ በላይ የሥራ እድሎች ተፈጥረዋል
ሚያዝያ 20 ቀን 2014 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ የሆርቲካልቸር ዘርፍ ከ200ሺህ በላይ የሥራ እድሎች መፍጠር መቻሉ ተገለጸ።
የኢትዮጵያ ሆርቲካልቸር አምራች ላኪዎች ማኅበር "የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የሆቲካልቸር ልማት ኢንቨስትመንት ማስፋፊያ" በሚል ያዘጋጀው የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
በምክክሩ በኢትዮጵያ በሆርቲካልቸር ዘርፍ ሰፊ የኢንቨስትመንት እድል መኖሩ የተነሳ ሲሆን በዘርፉ የሥራ እድል ፈጠራን ማስፋፋትና የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ይቻላል ተብሏል።
ለማሳየነትም በአሁኑ ወቅት ከ200 ሺህ በላይ የሥራ እድል መፈጠሩና ለዚህም የግሉ ዘርፍ ከፍተኛድርሻ እንዳለው ተገልጿል።
በዘርፉ ምርትም 17 ነጠብ 5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት መሸፈኑ በመድረኩ ተነስቷል።
የኢትዮጵያ ሆርቲካልቸር ምርቶች ከ80 በላይ ሀገራትም ገበያ ላይ በመቅረብ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ አስገኝተዋል።
ኢትዮጵያ የሆርቲካልቸር ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክ ከአፍሪካ አራተኛ ደረጃ መያዟም ተመልክቷል።
የአበባ ምርቶችን በመላክ ደግሞ ከኬንያ በመቀጠል በሁለተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ተገልጿል።
ወደ ውጭ ከሚላኩት የሆርቲካልቸር ምርቶች መካከል አበባ፣ ፍራፍሬ፣ የአትክልት ምርቶች ቅድሚያውን ይወስዳሉ።
በመድረኩ ላይ በዘርፉ የሚታዮ ችግሮችን በጎ እድሎች ዙርያ ጽሑፎች እየቀረቡ ይገኛል።