ቀጥታ፡

የኦሮሚያ ክልል ርዕስ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ሀዋሳ ገቡ

ሚያዝያ 20 ቀን 2014 (ኢዜአ)የኦሮሚያ ክልል ርዕስ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የሲዳማ ህዝብ የዘመን መለወጫ "ፍቼ ጫምባላላ" ክብረ በዓል ላይ ለመታደም ሀዋሳ ገብተዋል።

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በተጨማሪም አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ እና ሌሎች የክልልና የፌደራል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና እንግዶችም በበዓሉ ላይ ለመታደም ሀዋሳ ገብተዋል።

በሀዋሳ ዶሬ አየር ማረፊያ ሲደርሱም የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም