በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ግቢ እየተከናወነ ያለው የጓሮ አትክልት ልማት ከተሞች በምግብ ራሳቸውን ለመቻል እንዲሰሩ ትምህርት የሚሰጥ ነው

69

ሚያዚያ 19/2014 (ኢዜአ) በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ግቢ እየተከናወነ ያለው የጓሮ አትክልት ልማት ከተሞች በምግብ ራሳቸውን ለመቻል መሰራት እንዳለባቸው ትምህርት የሚሰጥ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ገለጹ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ9 ወራት እቅድ አፈጻጸም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ  በተገኙበት የተገመገመ ሲሆን፤ ከግምገማው በኋላም የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ግቢ እየተከናወነ ያለውን የጓሮ አትክልት ልማት ጎብኝተዋል፡፡

በስፍራውም በጠባብ ቦታዎች ላይ የተጣሉ የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሶችን በመጠቀም የተለያዩ የጓሮ አትክልቶች እየለሙ ሲሆን፤ ለአትክልቶቹ የሚውል የተፈጥሮ ማዳበሪያም እየተመረተ ይገኛል፡፡

በመሬት ላይ ከሚለሙ አትክልቶች በተጨማሪ የተለያዩ ቁሳቁሶችን በመጠቀም በግድግዳ ላይ የማልማት ሰራ እየተከናወነ መሆኑም እንዲሁ፡፡

በጉብኝቱ የተሳተፉ ከፍተኛ አመራሮች የአዲስ አበባ ከተማ ገዎች ቢሮ ኃላፊሙሉጌታ ተፈራና ያስሚን ዋሃብረቢ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ኃላፊ እንዲ ሁም ግርማ ሰይፉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ እንደሚሉት፤ የጓሮ አትክልት ልማቱ ከተሞች በምግብ ራሳቸውን ለመቻል መስራት እንዳለባቸው ትምህርት የሚሰጥ ነው ብለዋል፡፡

የጎሮ አትክልት ልማቱን ያገለገሉ የቤት ውስጥ ቁሳቁሶችን በመጠቀም በግድግዳ ላይና በጠባብ ስፍራዎች ማምራት እንደሚቻል ማዬታቸውን ጠቅሰው፤ ለዚህ ደግሞ "ቦታ የለኝም" ከሚል አስተሳሰብ መውጣት እንደሚገባም ተናግረዋል፡

ከዚህ አኳያ አመራሩ  አርአያ ሆኖ መስራት እንዳለበት የጉብኝቱ ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው አመራሩ የከተማ ግብርና የምርት አቅርቦትን በእጅጉ መጨመር እንደሚችል በአስተሳሰብ ደረጃ መያዝ እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

ይህን አስተሳሰብ ወደ ህብረተሰቡ በማውረድ በጠባብ ቦታ ላይ ለራሱ የሚሆን አትክልት እንዲያመርት መስራት እንደሚገባም ነው ያብራሩት፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ሚኒስትር ድኤታ የሆኑት አለምጸሃይ ጻውሎስ፤ በጽህፈት ቤቱ ግቢ መሬትን ብቻ ሳይሆን በቀላሉ የሚገኙ ቁሳቁሶችን በመጠቀም በግድግዳዎች ላይ ማምራት እንደሚቻል ማሳየት መቻላቸውን የገለጹት፡፡

ይህም ህብረተሰቡ በቦታ ሳይወሰን ለራሱ የሚሆን አትክልትና ፍራፍሬ በቀላሉ እንዲያመርት ትምህርት የሚሰጥ ነው ብለዋል፡፡

በጽህፈት ቤቱ ከሚገኘው ካፍቴሪያ ከሚወጣው ተረፈ ምርት ለአትክልቶቹ የሚሆን የተፈጥሮ ማዳበሪያ በግቢው ውስጥ እየተመረተ ስለመሆኑም ነው የተናገሩት፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም