ጃፓን ኢምባሲ ከ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ ያስገነባው ዮዎ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ

ሀዋሳ ሚያዚያ 19/2014 (ኢዜአ) ጃፓን ኤምባሲ በሲዳማ ክልል ወንዶገነት ወረዳ ከ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ ያስገነባው ዮዎ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ።

በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካካኦ /Ito Takakao/ እና የሲዳማ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

የጃፓን ኤምባሲ ለትምህርት ቤቱ ግንባታ  ከ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ማድረጉ ታውቋል።

የትምህርት ቤቱ ግንባታ እያንዳንዳቸው አራት የመማሪያ ክፍሎች ያሏቸው ሁለት ብሎኮችን ያካተተ ነው።  

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም