ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ ለጎዳና ተዳዳሪና አቅመ ደካሞች ማዕድ አጋሩ

228

ሚያዝያ 16 ቀን 2014 (ኢዜአ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ ለጎዳና ተዳዳሪና አቅመ ደካሞች በቤተ መንግሥት ማዕድ አጋሩ፡፡

የትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ የምሳ ግብዣ የተደረገላቸው 230 ጧሪ የሌላቸው አረጋውያን፣ የጎዳና ተዳዳሪዎች፣ቤተሰብ የሌላቸው ህፃናትና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው አቅመ ደካሞች ናቸው፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት ተሳታፊዎች ለኢዜአ እንዳሉት፤ ቀና ብለን አይተነው በማናውቀው ቤተ መንግስት የምሳ ግብዣ ስለተደረገልን እናመሰግናለን፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም