ኢዜአ የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ18 ህፃናት ማህበራዊ ድጋፍ አደረገ

133

ሚያዝያ 13 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ማህበራዊ ለሚያደርግላቸው 18 ህፃናት የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

በኢዜአ የሴቶችና ባለብዙ ዘርፍ ዳይሬክተር ወይዘሮ ታደለች ቦጋለ ተቋሙ በችግር ወስጥ የነበሩ 18 ህጻናትን በቋሚነት እየደገፈ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

የዛሬው ድጋፍም የትንሣኤ በዓልን በማስመልከት ልጆቹ ከወላጆቻቸው ጋር በደስታ እንዲያከብሩ አብሮነታችንን ለማሳየት ነው ብለዋል።

በዚህም ለ18ቱ ህጻናት ለእያንዳንዳቸው የ2 ሺህ ብር ድጋፍ መደረጉን ገልጸው፤ ድጋፉ በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ለህጻናቱ ደጋፍ እያደረገ የሚገኘው ከተቋሙ ሰራተኞች በሚያገኘው ወርሃዊ መዋጮ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም