በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በጦርነት ለተጎዱ ወገኖች የሚውል ከ17 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ - ኢዜአ አማርኛ
በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በጦርነት ለተጎዱ ወገኖች የሚውል ከ17 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ
ሚያዚያ 12 ቀን 2014 (ኢዜአ) በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በጦርነት ለተጎዱ ወገኖች የሚውል ከ17 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ።
በአሜሪካ ዳላስ የኢትዮጵያ ግብረ-ሀይል ከ16 ሚሊዮን 900 ሺህ ብር በላይ፣ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን በፍራንክፈርት ከ561 ሺህ ብር በላይ እና ሀዲያ አለም አቀፍ በዳያስፖራ ማህበር 221 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል።
የዳያስፖራ ተወካዮች የተሰባሰበውን ገንዘብ ለአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ዛሬ አስረክበዋል።
በቀጣይም የተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብሮችን በማዘጋጀት ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፋቸውን እንደሚቀጥሉ ተወካዮቹ ገንዘቡን ባስረከቡበት ወቅት አረጋግጠዋል።
የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ ዳያስፖራው አገሩንና ወገኑን ለመደገፍ እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀው ምስጋና አቅርበዋል።
ዳያስፖራው እያደረገ ያለውን ድጋፍ በቀጣይም አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ