ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ 200 ለሚደርሱ አቅም ደካሞች ማዕድ አጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ 200 ለሚደርሱ አቅም ደካሞች ማዕድ አጋሩ
ሚያዝያ 10 /2014(ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ መጪውን የፋሲካና የኢድ በዓል ምክንያት በማድረግ 200 ለሚደርሱ አቅም ደካሞች ማዕድ አጋሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት፤ ማዕድ ማጋራትና መተባበር የኢትዮጵያዊያን የቆየ እሴት ነው።
በመሆኑም እርስ በእርስ በመተባበር በመደጋገፍ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በጋራ መቅረፍ አለብን ብለዋል።
በዘላቂነት ደግሞ አንድነታችንን ጠብቀን ለችግሮቻችን መፍትሄ በጋራ መሥራት አለብን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።